ቅዱስ ሲኖዶሱ ከአጣብቂኝ የሚወጣው ወደ ሓዋሪያቱ ቀኖናና ቀዳሚያን አበው ውሳኔዎችን በማገናዘብ ተመልሶ ስሕተቶቹን ሲያርም፥ ኢቀኖናዊያን ሹመኞችን ሲሽር ብቻ ነው
በትግራይ ቤተክርስቲያን ዙሪያ አያገባህም አርፈህ ዝም በል የሚል አስተያየት ተሰጠኝ። ይህ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት የሚለውን የዶግማ ትምህርት የሚቃረን አባባል ነው። እንኳንስ ትግራይ ውስጥ ባለችዋ ቤተክርስቲያን ግብፅ፣ አርመን፣ ሶርያ፣ ህንድ፣ ኤርትራ ባለችዋ ቤተክርስቲያን እኩል ባለጉዳይ መሆኔን ማሳወቅ እፈልጋለሁ። ዘረኝነት በቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ የለውም። ቅዱስ ሲኖዶስም ራሱን ቢያጠራ ደስ ይለኛል። እኔን አትናገሩኝ እነ አባ ኢሳይያስን ብቻ ተናገሩልኝ አይባልም። ነውር ነው። ለሻረው ቀኖና ይቅርታ ይጠይቅ። ሲኖዶስ ራሱ ቀኖና ነው የሚሉ አንዳንድ የዋሃንን እየተመለከትኩ ነው። መጽሐፈ ሲኖዶስን ከሆነ ጥሩ ብላችኋል። የአምስት ኪሎውን ስብስብ ከሆነ ግን ተሳስታችኋል። ሲኖዶስ ራሱ ቀኖና ነው የሚለው አባባል የፈለገውን ዓይነት ውሳኔ ቢወስን ቀኖና አድርገህ ተቀበል እንደማለት ነው። ለምሳሌ ባለፈው ንጹሕ ኦሮሞ ሹመናል ብሎናል ሲኖዶስ። ስለዚህ ሲኖዶስ ቀኖና ስለሆነ ንጹሕ ኦሮሞ (የሌላ ዘር ያልተቀላቀለበት) መሾምን እንደ ቀኖና እንቁጠረው ይሆን?? ባለፈው እነ አባ ሳዊሮስ የኦሮሞና የብሔርብሔረሰቦች ሲኖዶስ ብለው 26 ሰዎችን ሹመው ነበር። ከዚያ ቅዱስ ሲኖዶስ አወገዛቸው። እንደገና በዐቢይ አማካኝነት ተደራደሩ። ሐምሌ ፱ ቀን ቅዱስ ሲኖዶስ ንጹሕ ኦሮሞ ሹመንላችኋል እንኳን ደስ አላችሁ አለን። ከዚያ አሁን ደግሞ እነ አባ ኢሳይያስ መንበረ ሰላማ ብለው 6 ሰዎችን ሾሙ። ቅዱስ ሲኖዶስ ባለፈው እንዳደረገው ተደራድሮ ንጹሕ ትግሬዎችን (የሌላ ዘር ያልተቀላቀለባቸውን) ይሾምልን ይሆን ይሆንን??? አባ ሰረቀ ያለው ልክ ነው ማለት ነው? ቅዱስ ሲኖዶስ የሾማቸው ንጹሕ ኦሮሞዎች ወደፊት እነርሱም የሚሾሙት ንጹሕ ኦሮሞ ነው የሚሆነው ወይ...