ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከማርች, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ከሊቢያ ውድቀት ኢትዮጵያ ምን መማር አለባት?

  ከሊቢያ ውድቀት ኢትዮጵያ ምን መማር አለባት? አገር የሚጠፋው በብዙ መንገድ ቢሆንም የሊቢያን አወዳደቅና የምዕረባዊያንን ሤራ በአጭሩ በመመልከት አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚካሄደው ማመሳከሩ መፍትሔውን ቶሎ እንድንፈልግ ይረዳናል ብዬ አምናለሁ። (አቶ ቱምሳ ዹጋ) መምህር ፋንታሁን ዋቄ “ኦርቶዶክሳዊነትና የሰይጣን መንግሥት በሚል ርዕስ ካሳተመው የትርጉም መጽሐፍ ምዕራፍ አንድ  በባለቤቱ ፈቃድ ተቀንጭቦ የተወሰደ። በትዕግስትና በማሰውተዋል ያንብቡ፣ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚካሄደው ሁለገብ ብጥብጥ ጋ ያገናዝቡ፣ ከዚያም ለአገራችን የሚበጀውን ሀሳብ እያመነጩ ለሕዝቡና ለሚመለከታቸው ባገኙት መንግድ ሁሉ ያጋሩ። ለአገርዎ ውለታ በመሥራት የደገሰውን ጥፋት ይቀንሱ። መልካም ንባብ የአገራት መንግሥታትን መውደቅና የሚጀመርው መሪዎች ከገዛ አገራቸው ሕዝብ ጋር በማይጣጣም አስተሳሰብ ሲመሩ ብቻ ሳይሆነ የአገራቸውን ፈቃድ ለመፈጸም በሚያደርጉት አርቆ አስተዋይነት ምክኒያት ኃያላን አገራት ሥጋት ከገባቸው በሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ነው። በኢትዮጵያ ያለው ሁለት መልክ አለው። የአገራችን ጠላት ራሳቸው የአገሪቱ ልሂቃን ሲሆኑ ሁለተኛው የውጭ ጣልቃ ገብነትን ባለመዋቅ ወይንም በጊዜዊ ጥቅም ተገዝተው የሚያገለግሉ የፖለቲካ ልሒቃን መንሰራፋት ነው።  የሊቢያ ግን በግልጽ መንግሥትን ከራሲ አገር ሕዝብ ጋር በማጋጨት የጣሉት ምዕረባዊያን ነቸው።   ለዚህ የሊብያን  ቀውስ  መመርመር ማስረጃ ነው፡-  ጋዳፊ ሥልጣን ከዯዘ በኋል፡-  1. ሕዝቡን ከበረሃ ችጋር አውጥቶ ዜጎችን ለከፍተኛ ሰላምና የኑሮ ደረጃው እንዲያድግ ያደረገውን መሪውን ሙሀመድ ጋዳፊን አስገደሉት 2. ይህን ተከትሎ ኢስላማዊ መንግሥትን (Islamic S...