ይህን ሰሞን ስለ ዓለማወ ዘፈንና ሙዚቃ የሚወዛገ ቡ መምህራኖችን ተመልክቻለሁ። እኔ የቀኖና ሊቅ አይደለሁም። ነገር ግን በሃይማኖት የማስብ ስለሚመስለኝ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ መስሎ ታየኝ። ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖትን ሕይወቱ ስላደረገ ሰውና ማኅበረሰብ ስንነጋገር የሰሞኑን ፖለቲካና ከመንፈሳዊ ዓላማ ውጭ የሆኑ ድብቅ ፍላጎታችን በተቻለ መጠን ያልተቀላቀለበት ትምህርት መስጠት ምእመናንን በማሳሳት ምክንያት ከበጎቹ ጌታ ከእየሱስ ክርስቶስ ቅጣት ያድናል። ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ በላይ የቅዳሴ የጸሎት ዜማን እስከነ ዓላማውና መንፈሳዊ ግቡ፥ ከእነ ጥልቅ ምሥጢሩ ተረድተን እንድናዜም ትፈልጋለች። ታስተምራለች፥ በተግባርና በህይወት ታሳያለች። በሂደቱ ሁሉ ህሊናችን፥ ዓይነ ልቦናችን እና መላው ተስፋችን ሁሉ ሰመያዊ ማንነታችንን አንጾ በመገኘት ላይ ታተኩራለች። ልጆቿም እንዲሁ በግልና በጋራ ድምፍ አውጥተው ወይንም በአርምሞ ሲያዜሙና ሲናገሩ ቅዳሱው ባመለከታቸው መሠረት ነፍሳቸውን ወደ ሰማዩ አባታቸው እንድታተኩር አድርገው ፈጣሪያቸውንና መድኀኒታቸውንን ክፍ ክፍ ማድረግና ማመስገን እንዲሆን እንደምታስተምር የቅዱሳን ሕይወት ሁሉ ይጠቁማል። ቤተ ክርስቲያን በግልጽና በአትቃላይ ዓለማዊ/ሥዝም ዘፈንን ኣታወግዝም። በመጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠን ምልክት በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል፦ ሮሜ 13፡13-14 “በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን። ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት። “ 1 ጴጥሮስ 4:3 “አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡