ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከኦገስት, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአማራ ሕዘብ የህልውናና የፍትህ ተጋድሎ የውስጥ እንቅፋቶች፦ በእኔ ምልከታ ፲ ናቸው

የአማራ ሕዘብ የህልውናና የፍትህ ተጋድሎ የውስጥ እንቅፋቶች፦ በእኔ ምልከታ ፲ ናቸው ። ሌሎችም ሊኖሩና በሌላ እይታ ሊብራራ ይችላል። እኔ ቁንጽልና አጭር ምልከታ ነው የማደርገው። በእርግጥ አሁን ባለው የትግሉ አውድ ሰዎች መወያየት የሚፈልጉት ጀግና እንዲሆንላቸው፥ ፋኖን ጠቅልሎ እንዲገዛላቸውና ከትጥቅ ትግል ማብቃት በኋላ የአገር ገዥዎች አድርጎ እንዲያነግሥሳቸው የሚሹ ወገኖች --- ጉዳይ ላይ መወያየት አይፈልጉም። ስለ ግለ-ሰብእና ስለ ቡድን ልዩነትና መበላለጥ፥ ማን ትክክል እንዳልሆነና እንደሆነ በመወጠር ስሜትን በሚቀሰቅስ፥ ማስበን በሚገድብ፥ ርቀት ከማየትን በሚጋርድ ድምጽ ውስጥ ሕዝቡን በራሳቸው ዙሪያ መሰብሰብ ይሻሉ።  እኔ ግን ጠቃሚ የሚመስለኝ ከግለሰቦችና ቡድኖች ጉዳይን አስቀድመን በመነጋገር ግለሰቦችና ቡድኖች ጉዳዮችን አንዳይጠልፉ፥ በተቃራኒው ለትግሉ ዓላማ፥ ፍልስፍና፥ ርእይ፥ ሂደት፥ ውጤት፥ የውጤት ዘለቃዊነትና የመስዋዕትነት መቀነስ አንጻ ብቻ እየተመዘኑ አንዲስተካሉ ማስገደድ/ማስተጋገልና ቀንበር ማስገባት ላይ ማተኮር ይመስለኛል።  በዚህ ማኅቀፍ ውስጥ የግል አስተያየት አጥቻለሁ!!! መወገድ ያለባቸው የትግሉ እንቅፋቶች፦ ( ፩ ) በአድዋ በቆሰሉ ቅኝ ገዥዎች፥ በአምላክ-የለሽ ማርክሳዊ ፖለቲካ ውድቀት ላይ የተወለዱት ሕወሃትና ኦነግ በሰፉት የ ዘ ረና የአፓርታይድ ሕገ - መንግሥት ውስጥ የተወለደው ትውለድ ከ1942ቱ የቀኝ ገዥዎች አእምሮ አጣቡ ትምህርት ቤት መከፈት ጀምሮ ብናስበው አሁን 70   ዓመታት የሚላው ነው። ሕወሃትና ኦነግ የ50 ዓመት ጎልማሶችን አፍርተዋል።  የአማራ ህልውና አደጋ ጥንስ ከ70 ዓመት አስቀድሞ የተጀመረና ባለፉት 50 ዓመታት ሕወሃት / ኢሕአዴግ ወደ ሕግና ፖ...

በቄስ አስተርአየ ጽጌ ፡ በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ መንግሥት ለሚፈጽመው ዘር ጥፋት ተጠያቂው ተወቃሹና ተከሳሹ ፓትርያርኩ ናቸው!

በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ መንግሥት ለሚፈጽመው ዘር ጥፋት ተጠያቂው ተወቃሹና ተከሳሹ ፓትርያርኩ ናቸው! ነሐሴ 2 ቀ 2016 ዓ/ም ቀሲስ አስተርአየ nigatuasteraye@gmail.com በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ መንግሥት ለሚፈጽመው ዘር ጥፋት ተጠያቂው ተወቃሹና ተከሳሹ ፓትርያርኩ እንደሆነ ቀኖናችን አጉልቶ ቢነግረንም፦ ቡራኬዎ ይደርብን የሚለውን ቄስና ዲያቆን በተለይም በጥጉ ከበውት ያሉትን ቀሳውስት ከተጠያቂነቱ ነጻ አያደርጋቸውም ፡፡ እንዴት? ምን ማድረግ ይችላሉ? የሰው ልጅ መንግሥት ባለመሠረተበት በPrimitive ዘመን ከውጭ በመጣበት ወራሪም ሆነ በእርስበርስ እልቂት የሞተው ሞቶ የተረፈው እንደገና በመባዛት ከማንሰራራት በቀር ለጠፋው ንብረት ተጠያቂ ካሳ ከፋይ የለውም፡፡ የፈሰሰውም ደምም ተጠያቂ የሌለው ደመ ከልብ ሆኖ ይቀር ነበር፡፡ በዚህ Primitive ዘመን savage በሚባለው ባህል ከላይ የጠቀስኩት አሰቃቂ ጥፋት ለረጅም ዘመናት በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ሲፈጸም ኖሯል፡፡ ከሚያጎራብቷት አገሮች ድንበሯን እየጣሱ በሚመጡት አረመኔወች አልፎ አልፎ ከሚደርሱባት ውዝግቦችና ቀውሶች በቀር ቀደም ብለው በመሰልጠን ከዚህ አስቃቂ ጥፋት ነጻ ከወጡት አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች፡፡      በምን ሂደት ነው ከሺዎች ዘመናት አረመኔዎች ሁሉ የባሱ የጎሣ ድርጅቶችና መንግሥት በኢትዮጵያ ሊፈጠሩ ቻሉ? ሕዘቡና ቤተክርስቲያን ከነባር ባህላቸው ያፈነገጡ አረመኔዎች አገሩን ሲቆጣጠሩ ምን አዘናጋቸው?   ኢትዮጵያ ከዐለምም ሆነ ካጎራባች አገሮች ይካሄድ ከነበረው ጸረ ሰብዕ ባህል ከረዥም ዘመን በፊት ቀድማ ልትላቀቅ የቻለቸው፦ ሕዝቦቿ በቋንቋቸው ቢለያዩም የተቀረጹባቸው መንፈሳውያን እሴቶቻቸው ከጎረቤት አገሮች የተለዩ በመሆና...